Friday, July 3, 2015

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ በአሜሪካ ግምገማ



--------------------



lor: white; clear: both; font-family: Nyala, 'Geez Unicode', 'GF Zemen Unicode', 'visual Geez Unicode', EthiopiaJiretRegular, Arial, Helvetica, 'Arial Unicode MS', sans-serif; font-size: 15px; line-height: 17px; margin: 0px; padding: 0px; width: 640px;">
 ዓርማየዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ዓርማ





የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትየዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ በአሜሪካ ግምገማ - ዘገባ ክፍል አንድ
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ በአሜሪካ ግምገማ - ዘገባ ክፍል ሁለት
የኢትዮጵያ መንግሥትና ባለሥልጣናቱ ባለፈው የአውሮፓ 2014 ዓ.ም ውስጥ በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን መፈፀማቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በብዙዎቹ አጋጣሚዎች ጥሰቶቹ የሚፈፀሙት በሕገመንግሥቱ ላይ የሠፈሩት ድንጋጌዎች እየተጣሱ መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ሪፖርት አመልክቷል፡፡
በመንደር ምሥረታ ላይ የቀረቡ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያረጋግጡ መረጃዎች አለመቅረባቸውን፤ ነገር ግን ለሰፋሪዎች የተገቡ ቃሎች አለመፈፀማቸውን ወይም መዘግየታቸውን ወይም የመሠረተ-ልማት አውታሮች ሳይዘረጉ ሰዎች እንዲሠፍሩ መደረጉን ሪፖርቱ አብራርቷል፡፡
በዘፈቀደ በሚካሄዱ የእሥራት አድራጎቶችና የእሥረኞች አያያዝ፣ የፍትሐዊ የፍርድ ሂደት መነፈግ፣ የግል የቤተሰብ፣ የቤት እና የመልዕክት ልውውጦች መደፈር፣ ሃሣብን የመግለፅ እና የፕሬስ ነፃነት፣ ትችትን ለማፈን የኢትዮጵያ መንግሥት የስም ማጥፋት ድንጋጌዎችን እንደመሣሪያ ስለመጠቀሙ፣ የኢንተርኔት ነፃነትና ባሕላዊ መድረኮች፣ በሰላም የመሰብሰብና የመደራጀት ነፃነት፣ በመንግሥቱ ውስጥ ያለ ሙስናና የግልፅነት መጓደል፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የፖለቲካ ተሣትፎ በሚሉ ክፍሎች የተጠናቀረ ነው ይህ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያለፈው የአውሮፓ ዓመት - 2014 ዓ.ም የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ግምገማ፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡

No comments:

Post a Comment